ሀገር በቀል ዛፎች

              ሀገር በቀል ዛፎች ማለት አዚሁ በሀገራችን ዉስጥ የሚበቅሉ አና በአሁኑ ወቅት አየተመናመኑ የመጡ ተክሎች ሲሆኑ አነዚህ ተክሎች በአሁኑ ሰዓት ሊመናመኑ የቻሉበት ምክንያት ዉስጥ ዋንኛ የምንለዉ የባህር ዛፍ ተክል መብዛት አንደሆነ ልናረጋግጥ ችለናል፡፡ የሀገር በቀል ዛፍ ከምንላቸዉ መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሱት ዉስጥ የአበሻ ጽድ ወይራ ግራር ቀጋ ኮሶ ኮርች ዕምበልባል እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

        የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር የእንጦጦ ተፈጥሮዓዊ ፓርክ /ቤት የችግኝ  ጣቢያ የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ እንደገለጹልን በአሁኑ ሰዓት የባህር ዛፍ የመብዛት ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ የእንጦጦ ተፈጥሮአዊ ፓርክ እየወሰደ ያለዉ እርምጃ የባህር ዛፍ ተክሎችን እየቆረጡ በማንሳት ሀገር በቀል የሆኑ ተክሎችን በመተካት ላይ እንደሚገኝ  ገልጸዋል፡፡

        የፕሮግጋሙ አስተባባሪ እንደገለጹት ከሆነ ፓርኩ በአሁኑ ሰዓት ከ 300 ሄክታር ቦታ ላይ ከፍታቸዉ ከ2600-3100 የሚደርስ ዛፎች እንዳሉት ገልጸዉ በተለይ የአፈሩ አይነት ሸክላማ አፈር የሚባለዉ በመሆኑ በተዳፋት አካባቢ በቀላሉ በዝናብ ታጥቦ ሊሄድ ስለሚችል እነዚህ ሀገር በቀል ዛፍ የምንላቸዉ አፈሩን በመያዝ ዝናብ አፈሩን እንዳይሸረሸረዉ እንደሚረዱን ተናግረዋል፡፡

        በአሁኑ ሰዓት በፓርኩ ዉስጥ ከ20 ዓይነት በላይ ሀገር በቀል ችግኞች እንደሚገኙና ዋን  አላማዉም አፈር እንዳይሸረሸር (የጎርፍ መጠን መቀነስ) እና የዱር እንስሳት እንዳይጠፉ የሚረዳ በመሆኑ ለዚህ አላማ ሀገር በቀል ዛፎች ዋን    አስተዋጽኦ እንዳላቸዉ ተናግረዋል፡፡

                                      ከሚኪያስ ገ/ጻዲቅ   

Post new comment

The content of this field is kept private and will not be shown publicly.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd> <b> <i> <blockquote> <img> <embed> <object>
  • Lines and paragraphs break automatically.

More information about formatting options

CAPTCHA
This question is for testing whether you are a human visitor and to prevent automated spam submissions.
Image CAPTCHA
Copy the characters (respecting upper/lower case) from the image.